ለቸኮለ! የዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 25/2011 አበይት ዜናዎች- ከዋዜማ ራዲዮ
1. በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ በመኖሩ ብቻ ቻይና ለኢትዮጵያ ያላት ፖሊሲ እንደማይቀየር ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሰታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ የ3 ቀናት ሥራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ዋንግ ይ ዛሬ ከአቻቸው ወርቅህ ገበየሁ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የወሰደቻቸውን የኢኮኖሚያ ማሻሻያዎች አደንቃለሁ ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዢ ፒንግ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ቻይና በመጭው ሚያዚያ በምታዘጋጀው ሁለተኛው Belt and Road የተሰኘው ዐለም ዐቀፍ ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ወክለው እንዲገኙ የጋበዟቸው መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ ሚንስተሩ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡
2. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው እና መለያ ቁጥሩ ET 338 የሆነው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ኢንቴቤ ዐለም ዐቀፍ አውሮፕላን ሲያርፍ ከመንደርደሪያው የመንሸራተት አደጋ ገጥሞታል፡፡ አደጋው በረራዎችንና ተጓዦችን አስተጓጉሉ እንደነበር የኡጋንዳው ዴይሊይ ሞኒተር ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው አውሮፕላን 139 ተጓዦችን ጭኖ ነበር፡፡ በተፈጠረው ችግር በተሳፋሪዎችና ሠራተኞችም ሆነ በአውሮፕላኑ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡ የችግሩ ምንጭ እየተጣራ ነው፡፡
3. የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ካሉት 19,500 ሰራተኞቹ ግማሽ ያህሉን አሰናበተ። ፎርቹን እንደዘገበው ከያዝነው ወር ጀምሮ ስምንት ሺ ያህል ሰራተኞችን እንዲቀጥሉ ቀሪዎቹ ግን ወደ ሌሎች ተቋማት እንዲዛወሩና የተወሰኑት ሙሉ በሙሉ ኮንትራታቸው ተቋርጦ እንዲሰናበቱ ተደረጓል።
4. የደምቢዶሎ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶር ገላሳ ቡልቻ ከደምቢዶሎ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ ባልታወቁ ሰዎች መታገታቸው ተሰማ። ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት ፕሬዝዳንቱ በጉዞ ላይ ሳሉ ድንገት ተሰውረዋል።
5. የመንግሥት ቤቶች ኮርፖሬሽን በቅርቡ ባደረገው የኪራይ ተመን ጭማሪ አተገባበር ላይ ማሻሻያ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ ይህ የተገለጸው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ረሻድ ከማል ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሆኑን ፋና ዘግቧል፡፡ አዲሱ ማስተካከያ ተከራዮች በመጀመሪያው ዐመት የጭማሪውን 35 በመቶ፣ በ2ኛው ዐመት 70 በመቶውንና በ3ኛው ደሞ ጠቅለው እንዲያጠናቅቁ ዕድል ይሰጣል፡፡ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለሐይማኖት ተቋማት፣ ለፓለቲካ ድርጅቶችና ለትርፍ ላልተቋቋሙ ድርጅቶች ቢሮ ኪራይ በካሬ 339 ብር የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 140 ብር ዝቅ ብሏል፡፡ ለኢምባሲዎች በካሬ 92 ብር የነበረው ወደ 50 ብር ወርዷል፡፡ ዝቅተኛው የኪራይ ተመን በካሬ 73 ብር ሆኗል፡፡
6. ትናንት ከሃላፊነት ተነስተዋል የተባሉት የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ብልለኔ ሥዩም እና ምክትላቸው ሔለን ዮሴፍ ከሃላፊነት አልተነሱም፡፡ ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ምንጮችን ጠቅሶ DW እንደዘገባው ሁለቱም ዛሬም በሥራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ ዘግቧል፡፡ በምክትል ፕሬስ ሴክሬታሪነት ተሹመዋል የተባሉት ካሳሁን ጎፌም የደረሳቸው የሹመት ደብዳቤ የለም፡፡ ፕሬስ ሴክሬታሪ ንጉሱ ጥላሁን ግን ሹመታቸው እውነት መሆኑን ለDW አረጋግጠዋል፡፡
7. የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ረቂቂ አዋጅ ለሕዝብ ተወካች ምክር ቤት መመራቱን ሸገር ዘግቧል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ከሙያተኞች እና ከባለ ድርሻ አካላት አስተያየት ሲሰጥበት ቆይቷል፡፡
ለሌሎች ያጋሩ SHARE SHARE
18 comments
እናመሰግናለን!!!
Tnx!
What’s DW?
Is it Deutsche Welle or Dimtsy Woyane?
If it’s the later please do me a big favor, don’t even bother yourself to reply, just block me.
Thanks Wazema for your great work.
እናመሰግናለን
A passenger reported: “ET338 almost crashed into Lake Victoria after running off the runway. All the people came out with mud on their feet.”
http://avherald.com/h?article=4c26482a
Enamesgnalin
Tnx
የእኔ 1ኛ የመረጃ ምንጭ ዋዜማ ነው።
ለቸኮለ እናመሰግናለን።
እናመሰግናለን !!!
Thank you so much, Dears!
ይመቻችሁ
4ቱ አየር መንገድ ህብረት የፈጠሩት ይህን ለማድረግ ከሆነ ሼም ነው በፍፁም አይሻሻሉም
Thanks !
Thanks ዋዜማ ራድዮ
ስለ metec የሰራተኞች ቅነሳ በተመለከተ ተጨማሪ ማብራራያ ካላችሁ pls
ሥረርዓት አልበኛው የገመቹ ገንፌ ቡድን ባለፉት አራት አመታት በኮንሶ ላይ በፈፀሙት ዘረፋ እና የመብት ጥሰት ተጠያቂ እንዳይሆኑ በተለያዩ የዞኑ አከባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በማደፍረስ እና የፀጥታና ፍትህ ተቋማትን አቅም በማዳከም የመንግስት እና ህዝብን ትኩረት በማስቀየስ እድሜያቸውን ለማራዘም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህን አፍራሽ ተግባር በመፈፀም እና ፖለቲካዊ ሽፋን በመስጠት ረገድ፣ እንዲሁም ሁኔታዎችን ይበልጥ በማጋነን በህዝብና በክልሉ መንግስት ላይ ከፍተኛ ውጥረት እና ጫና የሚፈጥሩት አክራሪ ብሔርተኛ አቋም በማራመድ አካባቢውን ወደ የለየለት ቀውስ ውስጥ ለማስገባት ላይ ታቹን እየማሱ ይገኛሉ።
ይሄው የገመቹ ገንፌ ቡድን አካባቢው ሁከትና ብጥብጥ እንዲቀሰቀስ፣ ብሎም እንዲባባስ በማድረግ በሚፈጠረው ግርግርና አለመረጋጋት አማካኝነት የፖለቲካ ስልጣን የመያዝ ዓላማና ግብ ለማሳካት ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል መንግስት ወደ አካባቢው ለሠላም ሥራው ብቅ ያሉ አመራሮች በአሉባልታ ስማቸውን በማጠልሸት ላይ ተጠምደው አወዛጋቢነታቸው ቀጥለውበታል። ይኸው ቡድን ከያዘው የተዛባ ዓላማና ግብ የተነሳ የሚወተውቱት በቀጥታ የክልሉ አመራር የለውጥ መሪዎች እንዳልሆኑ አስመስለው በማህበራዊ ሚድያዎች የአዞ እንባቸውን እያንጠባጠቡ ይገኛሉ። በተለይ መንግስት ከጥፋታቸው ይመለሳሉ በማለት ይቅርታ ተሰጥቷቸው ከተመለሱ ወዲህ በአካባቢ የኮንትሮባንድ ንግድ በበላይነት ከተቆጣጠሩ በወንጀል የሚፈለጉ የህወሓት እና የኦነግ ሸኔን የአካባቢው ጠርናፊዎች ጋር ሕብረት በመፍጠር በቀጠናው ትርምስ እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ቡርጅ፣ አማሮና በኦሮሚያ ሞያሌ የሀገሪቱ አከባቢዎች ወጣቶችን መልምለው በመላክ በውጊያውም ጭምር በመሳተፍ ሐገራዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት ችግር በመፍጠርና በማባባስ ራሳቸውን ከህግ ተጠያቂነት ለመታደግ እየታገሉ ያሉቱ አክራሪ ብሔርተኛ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት እየሠሩ ይገኛል።
በዚህ መሰረት የብሔርተኝነት አጀንዳ የሚያቀነቅኑት የፖለቲካ ቡድኖች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከህወሓት ጋር በትብብር በመስራት ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ከህወሓት የገንዘብና ማቴሪያል ድጋፍ ይደረግላቸዋል። በተለይ አክራሪ ብሔርተኝነት የሚያቀነቅኑት ነባርና አዳዲስ የፖለቲካ ቡድኖች ከድጋፍና ትብብር በዘለለ ከህወሓት ጋር ተመሳሳይ ዓላማና ግብ አላቸው። ይኸውም በየቦታው ሥርዓት አልበኝነትንና ትርምስ በማንገስ፣ ሕዝቡን በባህል ስም በመገዘተ ለሥልጣን ቁማር መደራደሪያነት በመለያየት አሁን ክልሎችን አየመሩ ያሉቱ የለውጥ ሐይሉ ሐገሪቱን መምራት እንዳልቻሉ ለማሳያነት በመጠቀም የሕወኃት አጀንዳ በማሳካት ላይ ተጠምደዋል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ብሔርተኛ ቡድኖች የራሳቸው የበላይነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ግብግብ ለሕዝቦች ጥቅምና ፍላጎት በፍጹም ደንታ የለላቸው ከመሆናቸውም በላይ እርስ በእርስ በሠለጠነው መንገድ የመነጋገር ባህልና ልማድ ማጣታቸው የተነሳ የቀረበላቸውን ተደጋጋሚ የሠላም ጥሪዎች ማምከን ዋነኛው የባህሪያቸው መገለጫ ነው።
በመሆኑም በደቡብ ክልል ኦሮሚያ ኩታ ገጠም አካባቢዎች በኦነግ ሸኔን የሚደረገውን ትርምስና ሥርዓተ አልበኝነት ግዲያዎች፣ ማፈናቀልና የንብረት ቃጠሎ በቅንጅትና በተግባር በመሳተፍ ላይ ያለው የገመቹ ገንፌ ቡድን ላይ የሕግ በላይነት ካልተረጋገጠ የአካባቢው ቀይ ቀጠናነት መንግስትን ከፍተኛ ዋጋ ስለሚያስከፍል ከወዲሁ ይታሰብበት እንለላለን፡፡
Comments are closed.