ለቸኮለ! የዛሬ ዓርብ ታህሳስ 26/2011 አበይት ዜናዎች -ከዋዜማ ራዲዮ

ለቸኮለ! የዛሬ ዓርብ ታህሳስ 26/2011 አበይት ዜናዎች -ከዋዜማ ራዲዮ

1. ከሶስት ቀናት በፊት ባልታወቁ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ደላሳ ቡልቻ (ዶ/ር) መለቀቃቸውን VOA ማምሻውን ዘግቧል:: ፕሬዝዳንቱ
ባልታወቁ ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አረጋግጫለሁ ሲል ተናግሮ ነበር፡፡ የጽህፈት ቤቱ ምክትል ሃላፊ ደሬሳ ተረፈ ዛሬ ለDW እንደተናገሩት ሰውዬው ከእነ ሹፌራቸው የታፈኑት ሃዋ ጋላን ወረዳ፣ በጋባ ሮቢ በተባለች ከተማ ነው፡፡ ስለ አፋኞቹ ማንነት ተጠይቀው በአካባቢው ትጥቅ ትግል እንካሂዳለን የሚሉ ቡድኖች መኖራቸውን ጠቅሰው ማንነታቸው ግን ገና እየተጣራ ነው ብለዋል፡፡

2. አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ የተሻሻለውን የአስተዳደሩን ሥራ አስፈጻሚ አካላት ረቂቅ አዋጅ አሻሽሎ በማጽደቅ 18 ተቋማትን አጥፏል፤ 5 ተቋማትን ደሞ እንደገና አደራጅቷል፡፡ ሙሉ በሙሉ ከታጠፉት መካከል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ካይዘን ኢንስትቲዩት፣ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የተቀናጀ መሬት መረጃ ማዕከል፣ የመለስ ዜናዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር፣ ሽግሽግና ኢንኩቤሽን ማዕከል እና የደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽህፈት ቤት ይገኙበታል፡፡ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን፣ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ግንባታ ኢንተርኘራይዝ እና የግንባታ ዲዛይን ጽህፈት ቤት ደሞ እንደገና ተዋቅረዋል፡፡

3. በወለጋ ነቀምቴ፣ ጊምቢ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ጸጥታ ለማስከበር የተቋቋመው ማዕከላዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) አንዳንድ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል፡፡ ቪኦኤ ከአካባቢዎቹ ምንጮችን ጠቅሶ ትናንት እንደዘገበው ሰዎቹ የተያዙት ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ተጠርጥረው ነው፡፡ ምን ያህል ሰዎች እንደተያዙ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ዕዙ ግን “አባ ቶርቤ” በተባለው ነፍሰ ገዳይ ቡድን ከሚጠረጠሩ ግለሰቦች ውጭ ሌላ ማንንም አልያዝኩም ሲል አስተባብሏል፡፡

4. የሕግ የበላይትን እና ሰላምን ለማረጋገጥ የሕዝብ ተሳትፎ በመሆኑ ሕዝቡ አስተዋጽዖ ያድርግ- ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ ተማጽኗል፡፡ የክልሉ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ታጣቂዎች ሳቢያ በአራት የወለጋ ዞኖች እና በምዕራብ ጉጅ ዞን አሁንም የሰው ሕይወት እየጠፋ ነው፤ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና መንገዶችም እንደተዘጉ ይገኛሉ፡፡ ጤና ጣቢያዎች ሥራ በማቆማቸው ወላድ እናቶች መንገድ ላይ ለመውለድ ተገደዋል፡፡ የውሃ እና መንገድ ፕሮጄክቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል፡፡ ሊሰብሩን የሚፈልጉ ሃይሎች “ኦሮሞ ሀገር መምራት አይችልም፤ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም” እያሉ ለውጡን ለማደናቀፍ እየሰሩ ነው ብሏል፡፡

5. የዲያስፖራ ኤጀንሲ የሕግና መዋቅር ዝግጅቴን ጨርሼ ወደ ሥራ ልገባ ነው ብሏል፡፡ ኤጀንሲው አሁን የሰው ሃይል በማሰባሰብ ላይ መሆኑን ዳይሬክተሯ ሰላማዊት ዳዊት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡ ኤጀንሲው ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ በውጭ ሀገራት ላሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ተዘጋጅቷል፡፡

SHARE SHARE ..ለሌሎች ያጋሩ! መልካም የዕረፍት ቀናት፣ መልካም በዓል!

Source

You might like

23 Comments

 1. The act of kidnapping the scholar by terrorists in # 1 is an act of cowardice !Totally unacceptable and hopefully will result in serious consequence .Hope he’ll be freed and rejoined his family,prayers

 2. Thanks for sharing us valuable information with official source! Really Wazema is improving its information sharing protocool from time to time! Keep it up

 3. ዲያስፖራ ኤጀንሲ የዲያስፖራውን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን አገራዊ ግዴታውንም እንዲወጣ ማትጋት ይኖርበታል ።ግዴታን እየተወጡ ነው መብትን መጠየቅ የሚያምረው ።ከደሐ አገር ላይ አምጪ ብቻ አይሰራም ።መስጠት ግድ ይላል ።

 4. ቄር ምንድነው በደማቹ የመጣውን ህዝባችን ዕንዳይማር ዕንይታከም ማድረግ ዕነዚህ እንኮን አገር ቤታቸውን አይመሩም ልብ በሉ አሰወግዱ ሀገራቹን ከጭራቆቾ( አባቡልጉ )ጠብቁ

 5. ጋላን ወረደ አይባልም አማርኛ ጠፈቶብህ አንደልሆነ እናውቃለን ስድብና አሽሙር አቁም። ገላን ወረደ ነው። ሌላው ደግሞ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,የኦሮሚያ ክልል ተማፅኗል ብለሀል ክልሉ አላለም ። ጥሪ ነው ነው ነው ያቀረበው ። ከመፅሀፋ በፊት አስብ ።

 6. ሥረርዓት አልበኛው የገመቹ ገንፌ ቡድን ባለፉት አራት አመታት በኮንሶ ላይ በፈፀሙት ዘረፋ እና የመብት ጥሰት ተጠያቂ እንዳይሆኑ በተለያዩ የዞኑ አከባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በማደፍረስ እና የፀጥታና ፍትህ ተቋማትን አቅም በማዳከም የመንግስት እና ህዝብን ትኩረት በማስቀየስ እድሜያቸውን ለማራዘም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህን አፍራሽ ተግባር በመፈፀም እና ፖለቲካዊ ሽፋን በመስጠት ረገድ፣ እንዲሁም ሁኔታዎችን ይበልጥ በማጋነን በህዝብና በክልሉ መንግስት ላይ ከፍተኛ ውጥረት እና ጫና የሚፈጥሩት አክራሪ ብሔርተኛ አቋም በማራመድ አካባቢውን ወደ የለየለት ቀውስ ውስጥ ለማስገባት ላይ ታቹን እየማሱ ይገኛሉ።

  ይሄው የገመቹ ገንፌ ቡድን አካባቢው ሁከትና ብጥብጥ እንዲቀሰቀስ፣ ብሎም እንዲባባስ በማድረግ በሚፈጠረው ግርግርና አለመረጋጋት አማካኝነት የፖለቲካ ስልጣን የመያዝ ዓላማና ግብ ለማሳካት ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል መንግስት ወደ አካባቢው ለሠላም ሥራው ብቅ ያሉ አመራሮች በአሉባልታ ስማቸውን በማጠልሸት ላይ ተጠምደው አወዛጋቢነታቸው ቀጥለውበታል። ይኸው ቡድን ከያዘው የተዛባ ዓላማና ግብ የተነሳ የሚወተውቱት በቀጥታ የክልሉ አመራር የለውጥ መሪዎች እንዳልሆኑ አስመስለው በማህበራዊ ሚድያዎች የአዞ እንባቸውን እያንጠባጠቡ ይገኛሉ። በተለይ መንግስት ከጥፋታቸው ይመለሳሉ በማለት ይቅርታ ተሰጥቷቸው ከተመለሱ ወዲህ በአካባቢ የኮንትሮባንድ ንግድ በበላይነት ከተቆጣጠሩ በወንጀል የሚፈለጉ የህወሓት እና የኦነግ ሸኔን የአካባቢው ጠርናፊዎች ጋር ሕብረት በመፍጠር በቀጠናው ትርምስ እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ቡርጅ፣ አማሮና በኦሮሚያ ሞያሌ የሀገሪቱ አከባቢዎች ወጣቶችን መልምለው በመላክ በውጊያውም ጭምር በመሳተፍ ሐገራዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት ችግር በመፍጠርና በማባባስ ራሳቸውን ከህግ ተጠያቂነት ለመታደግ እየታገሉ ያሉቱ አክራሪ ብሔርተኛ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት እየሠሩ ይገኛል።

  በዚህ መሰረት የብሔርተኝነት አጀንዳ የሚያቀነቅኑት የፖለቲካ ቡድኖች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከህወሓት ጋር በትብብር በመስራት ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ከህወሓት የገንዘብና ማቴሪያል ድጋፍ ይደረግላቸዋል። በተለይ አክራሪ ብሔርተኝነት የሚያቀነቅኑት ነባርና አዳዲስ የፖለቲካ ቡድኖች ከድጋፍና ትብብር በዘለለ ከህወሓት ጋር ተመሳሳይ ዓላማና ግብ አላቸው። ይኸውም በየቦታው ሥርዓት አልበኝነትንና ትርምስ በማንገስ፣ ሕዝቡን በባህል ስም በመገዘተ ለሥልጣን ቁማር መደራደሪያነት በመለያየት አሁን ክልሎችን አየመሩ ያሉቱ የለውጥ ሐይሉ ሐገሪቱን መምራት እንዳልቻሉ ለማሳያነት በመጠቀም የሕወኃት አጀንዳ በማሳካት ላይ ተጠምደዋል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ብሔርተኛ ቡድኖች የራሳቸው የበላይነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ግብግብ ለሕዝቦች ጥቅምና ፍላጎት በፍጹም ደንታ የለላቸው ከመሆናቸውም በላይ እርስ በእርስ በሠለጠነው መንገድ የመነጋገር ባህልና ልማድ ማጣታቸው የተነሳ የቀረበላቸውን ተደጋጋሚ የሠላም ጥሪዎች ማምከን ዋነኛው የባህሪያቸው መገለጫ ነው።

  በመሆኑም በደቡብ ክልል ኦሮሚያ ኩታ ገጠም አካባቢዎች በኦነግ ሸኔን የሚደረገውን ትርምስና ሥርዓተ አልበኝነት ግዲያዎች፣ ማፈናቀልና የንብረት ቃጠሎ በቅንጅትና በተግባር በመሳተፍ ላይ ያለው የገመቹ ገንፌ ቡድን ላይ የሕግ በላይነት ካልተረጋገጠ የአካባቢው ቀይ ቀጠናነት መንግስትን ከፍተኛ ዋጋ ስለሚያስከፍል ከወዲሁ ይታሰብበት እንለላለን፡፡

Comments are closed.