ባለስልጣኑ በበዓል ዋዜማ በመዲናዋ አራት የእሳት አደጋ መከሰቱን ገለጸ

ባለስልጣኑ በበዓል ዋዜማ በመዲናዋ አራት የእሳት አደጋ መከሰቱን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በገና በዓል ዋዜማ በተለያዩ አራት አካባቢዎች የእሳት እና አንድ ድንገተኛ አደጋ መከሰቱን የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ገለጸ።

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ከተከሰቱ አራት የእሳት አደጋዎች ውስጥ ሶስቱን በህብረተሰቡ ተሳትፎ መቆጣጠር ተችሏል።

አንደኛው የእሳት አደጋ ደግሞ በባለስልጣኑ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ነው ያሉት።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ በተከሰተው የእሳት አደጋ አንድ ቤት ሙሉ በሙሉ የተቃጠለ ሲሆን፥ በአደጋውም ከ4 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በዚሁ የበዓል ዋዜማ አንድ ግለሰብ ከመጠን በላይ ጠጥቶ በመጓዝ ላይ የነበረ ግለሰብ ቱቦ ውስጥ ወድቆ ጉዳት ማስተናገዱን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ውጭ ግን በዛሬው እለት ምንም አይነት አደጋ ሳይከሰት በሰላም መጠናቀቁን አቶ ንጋቱ ገልጸዋል።

Source: Fana Broadcasting

You might like

25 Comments

 1. በእሳት አደጋው ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የተቃጠለው ቤት ያሳዝናል።ይሄኔ በእለቱ በአልን ከነቤተሰቦቻቸው በሰላም ለማክበር የዋዜማው ዕለት ሽርጉድ ሲሉ ባጋጣሚ ያላሰቡት እሳት ተነስቶ ይሄን ሁሉ ውድመትና ጉዳት አድርሶባቸው ይሆናል!?

 2. ህዝቡ እርስ በርሱ እየተባላ ይሄ ባይፈጠር ነበር የሚገርመው ግን በዛሬው እለት ከዚህ ውጭ የ ተፈጠረ አደጋ የለም ነው ያላችሁት በቃ እያደር ይጨመራል ?

 3. ለመላው የ”ክርስትና” እምነት ተከታይ በሙሉ

  በዚህ ጊዜ እምታከብሯቸው በዓላት ባጠቓላይ (እንቑጣጣሽ , መስቐል , ገና , ጥምቐት , ፋሲካ ወዘተ) አንዳቸውም ባይብሊካል መሰረት እንደሌላቸው ታውቓላችሁን???

  የኢየሱስ ሐዋርያት በህይወት ዘመናቸው እኚን በዓላት አክብረው አያውቑም ብቻም ሳይሆን እነሱ በነበሩበት ዘመን እኚህ በዓላት አልነበሩም። ከጊዜ ኋላ ከፊሎቹ በፈረንጆቹ ሲፈጠሩ የተቐሩት አብዛኛው ደሞ የሀገራችን ምርቶች ናቸው።
  ባይብል በዓመት ውስጥ በዋናነት ለ3 በዓላት እውቕና ይሰጣል … እነርሱም
  1ኛ የቂጣ በዓል ወይም ፋሲካ (ፋሲካው ስቕለት ላይ እምትሉት ሳይሆን ሌላ የአይሁድ በዓል ነው።)
  2ኛ የሰባቱ ሱባኤ በዓል እና
  3ኛ የዳስ በዓል ናቸው። (ኦሪት ዘዳግም 16፥16 ላይ አንድ ላይ ተጠቕሰዋል … በተናጠል ደሞ ብዙ ቦታ) ከነዚህ መሀል አንዳቸውም ልክ ባይብል ላይ ይከበሩ በነበሩበት መልኩ በእናንተ ዘንድ አይከበሩም። እንደውም አብዛኞቻችሁ ስለነዚህ በዓላት አታውቑም። በነገራችን ላይ ኢየሱስም በምድር ቖይታው የፋሲካን (የቂጣ በዓል) እና የዳስ በዓልን እንደታደመ ባይብል ያስተምራል። ከዛ ውጪ አሁን እምታከብሯቸውን በዓላት ኢየሱስ አላከበረም … ሐዋርያትም አላከበሩም … ከሐዋርያት ኋላ የነበሩ እውነተኛ ክርስቲያኖችም አላከበሩትም።
  ያው በዚህ መልኩ እውነተኛ የሆነው የክርስትና እምነት በብዙ ሰርጎ ገቦች ስለተበረዘ ክርስቶስ ያስተማረው ትክክለኛ የክርስትና አስተምህሮ የቱ ነው እሚለው ላይ ጥናት አርጉ ለማለት ያህል ነው።

 4. A nation that celebrates holidays to the level of burning down its home up on itself, and drink till throwing oneself from cliff. So hot a celebration.

 5. ምነው እኔን እረሱኝ ሰክሬ ቀን 6ሰዓት ላይ
  ትቦ የገባሁ አሁን ከምሽቱ 2ሠዓት ላይ
  አይደለ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከትቦው
  አውጥተው እራሴን ሆስፒታል ያገኘሁት
  ምነው የኔን የማዘግቡት እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁ

Comments are closed.