የገና በዓል በሠላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል – የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

የገና በዓል በሠላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል
*******************************************
የ2011 ዓ.ም የገና በዓል በሠላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታውቋል፡፡

ታህሣሥ 29/2011 ዓ.ም በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የገና በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ኮሚሽኑ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ዝግጅቱን አጠናቆ ወደሥራ ገብቷል፡፡

በተለይም የገበያ ቦታዎችና የሠዎች እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እና በመዝናኛ ስፍራዎች አስፈላጊውን ቁጥጥር እና ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ስምሪት ማድረጉን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከበዓሉ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ደንብ መተላለፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የትራፊክ ቁጥጥር ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲከበር መላው የከተማችን ነዋሪዎች ለጸጥታ አካላቱ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮእንዲቀጥል ጥሪውን እያስተላለፈ ፤-ህብረተሰቡ የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 011-1-11 01 11፤011-1-26 43 59 011-1 01 02 97 ፤011-8-69 88 23፤011-8-69 90 15 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አሰታቋል፡፡

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞቱን ገልፃል ፡፡

Source: EBC Ethiopian Broadcasting Corporation

You might like

10 Comments

  1. * እኔ #የእግዚአብሔር #ልጅ እንድሆን- ኢየሱስ #የሠው #ልጅ ሆነ፤ * እኔ እኔ #እንድከብር- ኢየሱስ #ውርደቴን ተሸከመ፤ * እኔ #ጻድቅ እንድሆን- ኢየሱስ #ኃጥያት ተደረገ፤ * እኔ #ነፃ እንድወጣ- ኢየሱስ በሰዎች እጅ #ግፍ ተቀበለ፤
    * እኔ #እንድወለድ- ኢየሱስ #ሞተ፤ * እኔ #እንድታሰብ(በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳገኝ)- ኢየሱስ #ተተወ፤ * እኔ #ህይወትን እንዳገኝ- ኢየሱስ #የሞትን #ጣር አጥፍቶ ተነሳ፤ * እኔ ወደ #በረከት እድገባ- ኢየሱስ ስለእኔ #መርገም ሆነ፤ * እኔ #የእርሱ #ሙላት #ተካፋይ እንድሆን- ኢየሱስ ስለእኔ #ድሃ ሆነ፤ * እኔ #እንድወፈስ – ኢየሱስ ስለእኔ #ቆሰለ ፤ * እኔ #ይቅር እንድባል- ኢየሱስ ስለእኔ #ተቀጣ፤ ♥♥♥ስለዚህ….#ስለተደረገልኝ እና #ስለተሰጠኝ #እጅግ #የከበረ #ስጦታህ #አመሠግናለሁ!!!

Comments are closed.