Thursday, April 25, 2024
Home News ህዝበ ክርስቲያኑ ለሀገር ሰላም በተጠናከረ መልኩ እንዲሰራ የሀይማኖት መሪዎች ጥሪ አቀረቡ

ህዝበ ክርስቲያኑ ለሀገር ሰላም በተጠናከረ መልኩ እንዲሰራ የሀይማኖት መሪዎች ጥሪ አቀረቡ

by AddisDaily
14 comments

ህዝበ ክርስቲያኑ ለሀገር ሰላም በተጠናከረ መልኩ እንዲሰራ የሀይማኖት መሪዎች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የክርስትና እምነት ተከታዮች ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በመተባበር ለሀገር ሰላም በተጠናከረ መልኩ እንዲሰሩ የሀይማኖት መሪዎች ጥሪ አቀረቡ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነኢየሱስ ለእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፉት መልእክት ሁሉም ለሀገር አንድነት እና ሰላም መትጋት እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሀይማኖት መሪዎቹ በመልእክታቸው ኢትዮጵያ ከምንም ጊዜውም በበለጠ ሰላም የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ መሆኗን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እንዳሉት፥ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ትልቅ ጸጋዎች መካከል ሰላም ዋነኛው ነው።

በመሆኑም ሁሉም ሰላምን መንከባከብና መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
አሁን ላይ ሀገሪቱ ከገባችበት የሰላም እጦት እንድትወጣም ሁሉም መስራት አለበት ብለዋል።

ወጣቱ ትውልድም በመረጋጋት እና በሰከነ መልኩ የወደፊቷን የሀገሪቱን እጣ ፈንታ መወሰን ይኖርበታልም ነው ያሉት።

ሰላም ለመንፈሳዊ እና ስጋዊ እንቅስቃሴ ዋነኛ ዋስትና ነው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ናቸው።

ሰላም ጅማሮውን ከግለሰብ በማድረግ እስከ ሀገር ይሰፋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ እያንዳንዱ ዜጋ ከምንም በላይ ሰላም እንዲሰፍን መስራት እንደሚገባው ገልጸዋል።

በተጨማረም ዘረኝነትን በመጸየፍ ያለምንም መለያየት በሀገራችሁ መኖር አለባችሁ ያሉት ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ቤተሰቦችም ልጆቻቸውን ከዘረኝነት የጸዱ እና በአንድነት የሚያምኑ በማድረግ ማሳደግ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነኢየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ በበኩላቸው፥ የክርስቶስን የልደት በዓል ስናከብር አብሮነቱን ፍቅሩን እና ይቅርታውን እያሰብን መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል።

ዴሞክራሲ፣ ልማት እና ብልጽግና እንዲመጣም ሁሉም ይህን ማድረግ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

የሀይማኖት መሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ በተፈጠሩ ችግሮች ዙሪያም መንግስት በጀመረውና ሀገራዊ አንድነት እና ሰላምን ለማስፈን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ሁሉንም ማሳተፍ እንዳለበት ጠቁመዋል።

አሁን ላይ የተጀመረው ህግ የማስከብር ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆን የተመኙት የሀይማኖት መሪዎቹ ህዝበ ክርስትያኑ ሀይማኖታዊ እሴቱን እና ኢትዮጵያዊነቱን በሚያንጸባርቅ መልኩ በዓሉን እንዲያከብርም አባታዊ ምክራቸዉን ለግሰዋል።

በአፈወርቅ አለሙ

Source: Fana Broadcasting

You may also like

14 comments

Afework Welu January 6, 2019 - 11:56 am

አሜን ቅዱስ አባታችን

Michock Berhanu January 6, 2019 - 11:58 am

ይድረስ ለ #ኣብይኣሕመድ
#ክፍል፩
ኣብይ ኣሕመድ ከማንም በፊት እና ከማንም በላይ ሰፍ ብሎ የተቀበላቸውን የትግራይ ህዝብን ክደዋል። ዶ.ር. አብይ በተመረጠበት ሰሞን ከሶማልየ ክልል ወደ ትግራይ ካመራ በሁዋላ የተደረገ አካዳሚክ ጥናት እንደሚያሳየው በተለያዩ የትግራይ ከተሞች “ዶ.ር አብይ ትደግፈዋለ ወይ?” ለሚል ጥያቄ 96% “በጣም!” የሚል መልስ ሰጥተዋል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለይስሙላ የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ አይደሉም እያሉ ህዝባችንን በጅምላ ማጥቃት፣ ኣንገት ማስደፋት፣ ማዋረድ፣ ማስወንጀል፣ … ኣልፎ ተርፎም “ትግርኛ ተናጋሪ” ብለው የዘር ማጥፋት እስከማወጅ ደረሱ። ይህ ሁሉ በሳቸው ቀጥታ ትእዛዝ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። ልቡን ከፍቶ በደስታና በከፍተኛ እልልታ የተቀባላቸውን የትግራይ ህዝብ ኣስከፉት፣ በተከታታይ በየመድረኩ ህሊናውን ኣቆሰሉት፣ ከጠላቶቻችን አብረው በየመድረኩ በህዝባችን ላይ ኣፌዙ፣ ተራገሙ፣ ኣጥላሉ።

#ባጭሩ እሳቸውና አጠገባቸውን ሆኖው እሳቸውን የሚዘውሩ ምኒልካውያን በሁሉም የመንግስት ሚድያ ትግራዋይ በዳይ ሌላው ተበዳይ ኣድርገው በመሳል በአለም አቀፍ የዘር ማጥፋት እንዲፈፀም ካሉ 10 እርከኖች 8ኛ ላይ በመድረስ በህዝባችን ላይ የቻሉትን ያህል ቀሰቀሱ፣ ኣወጁ፣ በመላ ኢትዮጵያም “ትግሬዎች ናቸው እንደዚህ ያደረጉ” ተብሎ እንዲደመደም ኣደረጉ። ጠ.ሚሩ የትግራይ ህዝብ ለዘለዓለም እንዳይቀበላቸው የሆነው ከላይ የጠቀስኩዋቸው ነገሮች እንዳለ ሆኖ ህዝባችንን በጦር ጀት ከደበደበ የሸዓብያ መሪ እና ከ 50,000 በላይ ህዝባችን ያፈናቀለ ገዱ ኣንዳርጋቸው ጋር በመሆን እርስ በርሳቸው ሲሞካሹ፣ በህዝባችን ሲሳለቁና የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላቶቼ ከሚላቸው እጅና ጉዋንት ሆኖው እኩይ ድርጊቱ ሲመሩ ግን ደጉና ጀግናው ህዝባችን አንቅሮ ተፋቸው፤ ጠ.ሚሩም ያኔ political suicide ፈፀሙ። በአሁኑ ሰዓት ዶ.ር ኣብይ በትግራይ ህዝብ ከመንግስቱ ሀይለማርያም በላይ ይጠላል። ይህ የሆነው እና እንዲሆን ሌት ተቀን የሰራው ደግሞ ራሱ ዶ.ር ኣብይ ነው።

#ከህወሓት ባህሪ ኣንፃር ሲታይ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ ይሰጣል ብሎ መጠበቅ አስቸጋሪ ነበር። ህወሓት እንደሌሎች የኢህአደግ እህት ፓርቲዎች አንባገነን ፓርቲ ቢሆንም በአፍሪካ ባልተለመደ መልኩ ስልጣን ለዶ.ር አብይ በሰላማዎ መንገድ አስረክበዋል። ይህንን ማድረጉ ህወሓት ለኦሮሞ ህዝብ ያለው ትልቅ ክብር ያሳያል። ዶ.ር ኣብይ ልክ ለሀይለማርያም ደሳለኝ እንዳደረጉት ለህወሓትም በክብር ሸልመው መሸኘት ሲገባቸው “27 ዓመት በሙሉ ቆሻሻ ነበር” ከማለት አልፈው ሁሉም የኢህአደግ ችግር ለአንድ ድርጅት (ህወሓት) አሸክመው ከዛም የትግራይ ህዝብ ወንጀለኛ ህዝብ በማድረግ ህዝባችን የሚኒልክ ነጋዴዎች መሳቅያና መሳለቅያ እንዲሆን አድርገዋል። በዚህ አላበቁም።

#ዶ.ር ኣብይ ለህወሓት ባለስልጣናት በ3 መስመር ደብዳቤ ራሱ ወደ ትግራይ ከሸኛቸው በሁዋላ ውዝግብ ለመፍጠርና ህዝባችን አላስረክብም ብሏል ተብሎ እንዲጠቃ ሰዶ ማሳደድን መረጠ። ራሱ ያባረራቸው ሰዎች የትግራይ ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጥ ተመኘ። የህ ብቻ አይደለም! የትግራይ ህዝብን የገደሉና መንገድ የዘጉ እንዲሁም በቅማንት ላይ የዘር ማጥፋት የፈፀሙ የወንጀለኞች ሁሉ ምልክት የሆኑ የአዴፓ ባለስልጣናት የለውጥ ሀወርያ አድርጎ እያቀረበ የትግራይ ህዝብ ግና ሁሉም ቆጥሮ እንዲያስረክብ ዶ.ር ኣብይ ጠበቀ።

Michock Berhanu January 6, 2019 - 11:59 am

ይድረስ ለ #ኣብይኣሕመድ
#ክፍል፪
#ተጋሩ ይህ በሚኒልካውያን ሶፍትዌር እና በዶ.ር ኣብይ ሀርድዌርነት የሚመራ እኩይ ስራ ስንቃወም ጠ.ሚ ተጋሩ ኦሮሞን እየተቃወሙ ነው ለማስባል ትግራዋይ የኦሮሞ ልጅ ስልጣን በመያዙ ነው እየተቃወመህ ያለው የሚል ተከታታይ ጥሪ በማስተላለፍ ከምናከብረው እና አንዳች የታሪክ ቁርሾ ከሌለን የኦሮሞ ህዝብ ሊያቀያይሙን ጥረዋል። ህዝባችን በሚንልክ ሰነልቦና ያልተበከሉ ሀቀኛ የኦሮሞ ልጆች ስልጣኑ ይዘው ፌዴራሊዝሙ እንዲጠብቁት ቢማፀንም ጠ.ሚሩ ከፀረ ፌዴራሊስት ምኒልካውያን እጅና ጉዋንት ሆኖው በመቶሺዎች መስዋእት ከፍለን የተከለነው ፌዴራሊዝም መናድና የትግራይ መሬትን ቆርሰው ለሚኒልካውያን ለማስረከብ “የክልሎች ወሰን፣ የአስተዳደርና ማንነት የሚያጠና ኮምሽን” ህገ ወጥ አዋጅ አፅድቀዋል። የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ገብሮ አንዳችና ትልቅዋ ፌዴራሊስት ኦሮሚያ ለኦሮሞ ህዝብ በኩራት ሲያስረክብ እሳቸው ግን በኦሮሞ ህዝብ ስም ወደ ስልጣን ተቆናጥጠው የትግራይ መሬትን ቆርሰው ለምኒልካውያን ለመስጠት ሽር ጉድ እያሉ ይገኛሉ።

#እናም አሁን ክቡር ጠ.ሚር ትላንት ” ሚሳኤል የሆኑ ቃላት በሚድያ እየወረወርን የትግራይ ህዝብ እንዳናጣው …” ያሉት አስቂኝና ኣናዳጅም ነው። አስቂኙ በገዛ ባልተገራ ሚድያቸው፣ አንደበታቸው እና ድርጊታቸው ህዝባችን ኣንቅሮ ከተፋቸውና በጣም ከጠላቸው በሁዋላ ህዝቡ እንዳናጣው ማለታቸው ነው። አናዳጅ የሚያደርገው ደግሞ ከፀሀይ በታች ያሉ የትግራይ ህዝብ ጠላቶችን ሰብስቦና ኣማክሮ ፀረ ትግራይ ህዝብ የፈለጉትን ካደረጉ በሁዋላ ስንት ተመክሮና ጥልቅ የፖለቲካ ልምድ ያለው የትግራይ ህዝብ እንደ ህፃን ለመሸወድ “ህዝቡ እንዳናጣው” ብለው ማፌዛቸውን ነው። ስለሆነም ክቡር ጠ.ሚ እንደ ጀመሩት ምኒልካውያን ይዘው በመንጎድ ጉዛቸውን ይጨርሱ። እባኩዎ እኛ ቤታችን ውስጥ ዝም ብለን ስራችን እየሰራን ስለሆነ አይነካኩን። በቆሰለ ቁስላችን እንጨት መስደድ ያቁሙ። በግብፅ፣ በሸዓብያና በሚንልካውያን ታጅበው ፀረ ትግራይ ህዝብ ስለተንቀሳቀሱ ህዝባችን “ህግ ይከበር ” ሲል ኦሮሞ ስለሆንኩ እየተቃወሙኝ ነው ማለታቸውንም በአስቸኩዋይ ያቁሙ። ከቻሉ 3ቱም አጃቢዎቻቸውን አራግፈውና የነሱን ሀሳብ ጥለው በኦሮሞ ህዝብ አስተሳሰብ፣ በአባገዳዎች ስነ ስርዓት፣ በአጠቃላይ ደግሞ ህግና ፌዴራሊዝምን አክብረው ለመምራት የመጨረሻ እድልዎን ይሞክሩ።
#ማሳሰብያ
የምንወዳቸው ውድ ሰማእታቶችቻን ገብረን የተከነልው ህገ መንግስትና ፌዲራሊዝም ሲናድ ቆመን እንደማናይ እንድታውቁልን እንፈልጋንለ።

ተጻፈ በኪዳነ ኣመነ
ዓረና ዲሞክራሲ እና ሏላዊነት ፓርቲ።

Fikre Z Bhere Ethiopia January 6, 2019 - 11:59 am

አሄሄሄ የእናንተ አባትነት!

Dawit Dawit January 6, 2019 - 11:59 am

ያልታወቀበት አሸባሪ ነው

Destaw Fetene January 6, 2019 - 12:11 pm

ድንቄም አባት አይይይይ….

u1264u1272 u1200u12edu1208 January 6, 2019 - 12:18 pm

በነገራችን ላይ ተስፋዬ ኡርጌ የጦስ ዶሮ ሆኗል ብዬ ማመኔን ይፋ ማድረግ እፈልጋለሁ። ከሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ከታሰ ረ አምስት ወር አልፎታል፤ እስካሁን መደበኛ ክስ አልተከፈተበትም። እያሰብኩ ያለሁት ምናልባት ለውጡን ባለመደገፉ ‘እሱ ነው እንዲህ የሚያደርገው’ በሚል ነው የታሰረው። በኋላ ደግሞ ‘ካፈርኩ አይመልሰኝ’ በሚል ነው እያቆዩ ያሉት። “ወንጀሉ ውስብስብ ነው፤ ማስረጃ አላገኘሁም” የሚሉ የፍትሕ ፀር ሰበብ አስባቦች ከፍትሕ አካላቱ ውስጥ ያለክፍያ ቢሰናበቱ ጥሩ ነው።
befikadu z.hailu
ለተስፋዬ አራጎም እንኳን አደረስዎ

Alemi Habita January 6, 2019 - 12:29 pm

መጀመሪያ። ከቤተክርስትያን ትጽዳ ህዝባችን ማይጸዳበት ምክንያት የለም

Yene Dagi January 6, 2019 - 12:37 pm

ደብረ ፂዎንን የሸለመው ከሆነ አዎ አንዳትሉኝ፡፡

Ayenew Hailu January 6, 2019 - 12:48 pm

Illegitimate!!

Yenanesh Hebesha January 6, 2019 - 1:46 pm

ያገር ሰላምን እያደፈረሳችሁ ያላችሁት እናተ ስለሆናችሁ መጀመርያ እናተ ፅዱ ከቅድስት ቤተክርስቲያን የተሀድሶ መልክተኞች ዘረኞች ዘራፊዎች…..ይፅዱልን። ቁልፍ ቁልፍ ቦታውን እናተ ተሰግስጋችሁ በየት ሰላም ፍቅር አድነት ይምጣ
ስይቀጥል ፀጋው ያለው አባት ከወረቀት እያነበበ አይናገርም።
የ ዘ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትራሪክ ብዕፁ አቡነ መርቆርዮስ ናቸው። እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛላቸው !!!

Worku Tolcha January 6, 2019 - 2:28 pm

ትላትናም ይህን ነበር ምንባለው ከትናቱ የተለየ ነገር የለውም

Easete Gabriel January 6, 2019 - 3:28 pm

እንኳን አብሮ አደረሰን

Amdemariam Mache January 6, 2019 - 3:34 pm

When celebrating Christmas, let us think the central doctrine of Christianity, that is ” love your neighbor ” – not ” love your ethnic group “.

Comments are closed.