ኮሚሽኑ በዓሉ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የገና በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ በተለይም በገበያ ቦታዎች እና የሰዎች እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ቦታዎች እንዲሁም በመዝናኛ ስፍራዎች አስፈላጊውን ቁጥጥር እና ጥበቃ ማድረግ የሚያስችል ስምሪት ማድረጉን አስታውቋል።
ከበዓሉ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ የደንብ መተላለፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የትራፊክ ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
ህብተሰቡም በዓሉ በሰላም እንዲከበር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያድርግም ጥሪውን አቅርቧል።
የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት አልያም አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥምም በ991 ወይም 816 የነጻ ስልክ መስመሮችን እንዲሁም፤ 011 869 83 23፣ 011 869 90 15 መጠቀም ይቻላል ብሏል።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮችን በዓሉ የሰላም እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
10 comments
የቀን ጅብ ሾልኮ እንዳይገባባቹ አደራ!!!
አብሽር !!! እኛም ስፍራችንን ከቀን ጅቦች ነቅተን እንጠብቃለን ኮሚሽንዬ !!!በዛው እንኳን አደረሰህ።
ወንጀል መከላከልና በተለይ ትራፊክ ቁጥጥር ስራችሁን በጣም ጥሩ ነው በርቱ!
ለራሱ ሳይጠብቅ በየትኛው አቅሙ ነው ህዝብ የሚጠብቀው ምፅ ምፅ…
Habtamu Gebre Selasi ሀብትሽ አነኳን አደረሰህ ወንድሜ በዓልን ያላንተ ማክበር በጣም እ.ህ.ህ…ብዬ ባለቅስ ምን ትለኛለህ ???ነገር ግን አላለቅስማ ። ምክንያቱም …
እግዜር ይጠብቀን እንጂ እናንተን አምነን እማ …..
የገዛሁትን ዶሮ ሲሰርቁኝ ፖሊስ ምን ሲሰራ ነበር?
ኢትዮጽያ የእለት ዳቦ እንኳ ማግኘት አቅቶአታል በኑሮ ውድነት ምክኒያት ግን እነኚህ በዓል በዓል ይላሉ ተኩላዎች ሁላ።
ነገ ጥምቀት ወይም መስቀል አይደለም ። የቤት እና የቤተ እምነት ውስጥ እንጂ የአደባባይ በአል አይደለም፤ ወይስ በያንዳንዱ ቤት ፖሊስ ሊመደብልን ነው?
እኔ ያሰለቸኝ ነገር ወሬ ፡፡ ይህን በተባለ ማግስት ማንነቱ ያልታወቀ ከባድ ወንጀል ፈጸመ የሚል ዜናአንሰማለን የፈጠረን አምላክ ይጠብቀን የእናንተን ተውት፡፡ሳታወሩ ለህሊናችሁ ስሩ እስኪ ዶ/ር አብይን አግዙት አንድ ጊዜ እንጅ ዘላለም አይኖር ሁሉም ጠፌ አላፊ ነው በዓሉ የሰላም ይሁንላችሁ፡፡ አሜን
Comments are closed.