Home News የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመላ ሃገሪቱ እየተከበረ ነው

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመላ ሃገሪቱ እየተከበረ ነው

by AddisDaily
3 comments

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመላ ሃገሪቱ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት (ገና) በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሃገሪቱ እየተከበረ ነው።

በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በተለይም በላል ይበላ ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች መከበር ጀምሯል።

በርካታ የእምነቱ ተከታዮችም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በማህሌት እና ቅዳሴ ሌሊቱን አሳልፈዋል።

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ ዐብይ በዓላት ውስጥ አንደኛው ነው።

የሃይማኖት መሪዎች በዓሉን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የክርስትና እምነት ተከታዮች ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በመተባበር ለሀገር ሰላም በተጠናከረ መልኩ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነኢየሱስ፥ ለእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፉት መልእክት ሁሉም ለሀገር አንድነት እና ሰላም መትጋት እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሀይማኖት መሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ በተፈጠሩ ችግሮች ዙሪያም መንግስት በጀመረውና ሀገራዊ አንድነት እና ሰላምን ለማስፈን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ሁሉንም ማሳተፍ እንዳለበት ጠቁመዋል።

Source: Fana Broadcasting

You may also like

3 comments

James Ye Hussen Lij January 7, 2019 - 6:15 am

ምነው ዘገያችሁ? ከሁመራ መልስ ነው?

Endale Sheferaw January 7, 2019 - 6:23 am

እናመሰግናለን!….. እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!

Alex Z Gonder Amhara January 7, 2019 - 6:32 am

#የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል………ብትሉስ ምናባታችሁ ትሆናላችሁ

Comments are closed.