ለቸኮለ! የዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 30/2011 አበይት ዜናዎች- ከዋዜማ ራዲዮ
1. ጦር ሃይሉን እንደገና የባሕር ሃይል ባለቤት ለማድረግ አንዳንድ ሥራዎች መጀመራቸውን የመከላከያ ሚንስትር አይሻ መሐመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ከኬንያ እና ፈረንሳይ የባህር ሃይል አደረጃጀት ልምዶች ተወስደዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት አስፈላጊ ፈተናዎችን ማለፍ ያልቻሉ ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሠራዊቱ አባላት በጡረታ ተገልለዋል፡፡ ሚንስትሯ ዛሬ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የመንፈቅ ሪፖርት ሠራዊቱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በግጭት ሳቢያ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው መልሶ እያቋቋመ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
2. ሳዑዲ የኢትዮጵያዊያን ቤት ሠራተኞችን መነሻ ደመወዝ 1 ሺህ ሪያል ለማድረግ ተስማምታለች፡፡ ደመወዝ ወለሉ ከፍ ያለው የማሕበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከሳዑዲ አቻቸው ጋር ታህሳስ 28 ቀደም ሲል የተፈረመውን የሠራተኛ ስምምነት ውል አፈጻጸም አስመልክተው በደረሱት መግባባት መሠረት መሆኑን የመንግሥት መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡ የሠራተኞች መብት ስለሚጠበቅበት ሁኔታም መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ የውሉን አተገባበር በየ6 ወሩ የሚገመግም የጋራ የባለሙያዎች ቡድንም ይቋቋማል፡፡
3. ተቀማጭነቱ የተባበሩት ኢምሬቶች የሆነው “አል ማክቱም” ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ለአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች ጋራ ጉሪ የሚል ስያሜ የተሰጠው ትምህርት ቤት መክፈቱን አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል፡፡ ትምህርት ቤቱ የተከፈተው የካ ክፍል ከተማ ውስጥ ሲሆን ከ5ኛ እስከ 9ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል፡፡ ለመጭዎቹ 5 ዐመታት የመምህራንን ደመወዝ ፋውንዴሽኑ ይሸፍናል፡፡ ከሚቀጥለው ዐመት ጀምሮ ደሞ ጎበዝ ተማሪዎች ነጻ የውጪ ትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ታቦር ገብረ መድኅን ተናግረዋል፡፡
4. የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች መቻቻልን እና ሰላምን ለመስበክ ያንድ ሳምንት የሰላም አዋጅ አውጀናል ብለዋል፡፡ አዋጁ ከትናንት ጀምሮ እስከ መጭው ዕሁድ ይቆያል፡፡ በሳምንቱ ሰላም እና መቻቻልን የሚያጠናክሩ የተለያዩ የውይይት መርሃ ግብሮች ይኖራሉ፡፡
5. በደቡብ ክልል የሚገኘው አባያ ሐይቅ በእንቦጭ አረም መጠቃቱን የጋሞ ዞን አካባቢ ጥበቃና ደን ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ኢዜአ እንደዘገበው እንቦጭ በሐይቁ ላይ መታየት የጀመረው በ2009 ዓ.ም ሲሆን ባሁኑ ሰዓት 2000 ሄክታር ያህል የሐይቁ ክፍል በአረሙ ተሸፍኗል፡፡ ካሁን ቀደም 10 ሺህ ሕዝብ በማስተባበር 30 ሄክታር ለማጽት ተችሎ ነበር፡፡
ለሌሎች ያጋሩ SHARE SHARE SHARE
Source: Wazema Radio ዋዜማ ሬዲዮ Facebook
6 comments
ምነው ሁላችን ብንማርበት በአም አቀፍ ወይም አገር አቀፍ ቋንን ቢያደርጉት
=============*========*===========
ተቀማጭነቱ የተባበሩት ኢምሬቶች የሆነው “አል ማክቱም” ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ለአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች ጋራ ጉሪ የሚል ስያሜ የተሰጠው ትምህርት ቤት መክፈቱን አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል፡፡ ትምህርት ቤቱ የተከፈተው የካ ክፍል ከተማ ውስጥ ሲሆን ከ5ኛ እስከ 9ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል፡፡ ለመጭዎቹ 5 ዐመታት የመምህራንን ደመወዝ ፋውንዴሽኑ ይሸፍናል፡፡ ከሚቀጥለው ዐመት ጀምሮ ደሞ ጎበዝ ተማሪዎች ነጻ ትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ታቦር ገብረ መድኅን ተናግረዋል፡፡
Thankyou
ኦሮምኛ የሀገራችን ብሔራዊ ቋንቋ ቢሆን ለኢትዮጵያ ሰላም የጎላ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ይድረስ ለአለምነህ በዚህ ዜና ተራ ቁጥር 4 ጉጅ የሚለው ጉጂ በሚል ቢስተካከል ።
ባህር ሃይል በክራይ ባህር ይቻላል እንዴ? የባህር ክራይ ክፍያ ቀን ሲያልፍ መርከቡን ጫት መቃሚያ እና ባህር ኃሎቻችን ካዳሚያቸው ነው ሚሆኑት? ተው እንጂ አታስቁን አታሳቁን በሏቸው
Tnx!
Comments are closed.