በፕሪሚየር ሊጉ ሃዋሳ ከተማ እና መቐለ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 29፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።
ክልል ላይ በተደረጉት ሁለት ጨዋታዎች ሃዋሳ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ ድል ቀንቷቸዋል።
ሃዋሳ ከተማ በሜዳው ጅማ አባ ጅፋርን አስተናግዶ 3 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።
አዳነ ግርማ፣ ታፈሰ ሰለሞን እና እስራኤል እሸቱ የድል ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ፥ ማማዱ ሲዴቤ ለጅማ አባ ጅፋር የማስተዛዘኛዋን ጎል አስቆጥሯል።
በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው መቐለ ከተማም በተመሳሳይ 3 ለ 1 አሸንፏል።
ያሬድ ከበደ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ እና አማኑኤል ገብረሚካኤል ለባለሜዳው ሲያስቆጥሩ፥ አዲስ ግደይ ደግሞ የሲዳማ ቡናን ማስተዛዘኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል።
ሊጉን ኢትዮጵያ ቡና በ18 ነጥብ ሲመራው ሃዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ይከተሉታል።
ስሑል ሽረ፣ ደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት ደግሞ የደረጃው ግርጌ ላይ ይገኛሉ።
10 comments
Enderta my heart beat
ሀዋሳ ከነማ አንደኞች
ስፖርታዊ ጨዋነት ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው
ዛሬ
መቐለ ♥ አሸነፍን
መቀለ
ምንጊዜም ቀዳሚ የሰላም፣ የፍቅር፣የመከባበር ተምሳሌት መቀለ – ትግራይ ሁሌም መሪ ሁሌም አሸናፊ፤ viva Tigray.
Ethiopia Bunna is the Best all are the Rest!. I celebrate Bunna! I sing Bunna!..I love Bunna n its passionate n colorful fans. I love Bunna n its style of play. I love Bunna players the old n the new. I love Bunna colors the yellow n the burgundy.
፣
ኳሱን ወደ ዘር የሚወስድ ጉድ በዝቷል፣
ድሬደዋ ተወልዶ ለወልዋሎ
አዳማ ተወልዶ ለፋሲል ከነማ የሚደግፍ የዘር በሽተኛ እየታዘብን ነው
ጠንካራው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ
Comments are closed.