ባለስልጣኑ በበዓል ዋዜማ በመዲናዋ አራት የእሳት አደጋ መከሰቱን ገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በገና በዓል ዋዜማ በተለያዩ አራት አካባቢዎች የእሳት እና አንድ ድንገተኛ አደጋ መከሰቱን የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ገለጸ።
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ከተከሰቱ አራት የእሳት አደጋዎች ውስጥ ሶስቱን በህብረተሰቡ ተሳትፎ መቆጣጠር ተችሏል።
አንደኛው የእሳት አደጋ ደግሞ በባለስልጣኑ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ነው ያሉት።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ በተከሰተው የእሳት አደጋ አንድ ቤት ሙሉ በሙሉ የተቃጠለ ሲሆን፥ በአደጋውም ከ4 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በዚሁ የበዓል ዋዜማ አንድ ግለሰብ ከመጠን በላይ ጠጥቶ በመጓዝ ላይ የነበረ ግለሰብ ቱቦ ውስጥ ወድቆ ጉዳት ማስተናገዱን ጠቅሰዋል።
ከዚህ ውጭ ግን በዛሬው እለት ምንም አይነት አደጋ ሳይከሰት በሰላም መጠናቀቁን አቶ ንጋቱ ገልጸዋል።
25 comments
ለምን አስካሪ መጠጦች አይታገዱም
ለምን መጠጥ ቤቶች ከ990ml በላይ ለአንድ ሰው ይሸጣሉ ……
የወያነ እጅ አለበት
ብዙ ሰው ለምን በደንብ አጠጣም?
እምነቱ እረሱ ስከርን ይፈቅደል
ይሄም ልማዳቹ የወያኔ እጅ ኣለበት በሉ ክክክክክክክ!!!
የወያኔ እጅ አለበት።
“በአ.አ ከተማ አንድ ሰው ሰክሮ ወድቀዋል”።ክክክክክክክክ የአመቱ ከባድ ዜና።ወይ FBC.KKKKKKKKKKKKK
በእሳት አደጋው ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የተቃጠለው ቤት ያሳዝናል።ይሄኔ በእለቱ በአልን ከነቤተሰቦቻቸው በሰላም ለማክበር የዋዜማው ዕለት ሽርጉድ ሲሉ ባጋጣሚ ያላሰቡት እሳት ተነስቶ ይሄን ሁሉ ውድመትና ጉዳት አድርሶባቸው ይሆናል!?
One Fire case has happened @ Asko today.
ህዝቡ እርስ በርሱ እየተባላ ይሄ ባይፈጠር ነበር የሚገርመው ግን በዛሬው እለት ከዚህ ውጭ የ ተፈጠረ አደጋ የለም ነው ያላችሁት በቃ እያደር ይጨመራል ?
ወያኔ የገነባት ከተማ አብይ እያፈረሳት ነው ።
ለመላው የ”ክርስትና” እምነት ተከታይ በሙሉ
፡
በዚህ ጊዜ እምታከብሯቸው በዓላት ባጠቓላይ (እንቑጣጣሽ , መስቐል , ገና , ጥምቐት , ፋሲካ ወዘተ) አንዳቸውም ባይብሊካል መሰረት እንደሌላቸው ታውቓላችሁን???
፡
የኢየሱስ ሐዋርያት በህይወት ዘመናቸው እኚን በዓላት አክብረው አያውቑም ብቻም ሳይሆን እነሱ በነበሩበት ዘመን እኚህ በዓላት አልነበሩም። ከጊዜ ኋላ ከፊሎቹ በፈረንጆቹ ሲፈጠሩ የተቐሩት አብዛኛው ደሞ የሀገራችን ምርቶች ናቸው።
ባይብል በዓመት ውስጥ በዋናነት ለ3 በዓላት እውቕና ይሰጣል … እነርሱም
1ኛ የቂጣ በዓል ወይም ፋሲካ (ፋሲካው ስቕለት ላይ እምትሉት ሳይሆን ሌላ የአይሁድ በዓል ነው።)
2ኛ የሰባቱ ሱባኤ በዓል እና
3ኛ የዳስ በዓል ናቸው። (ኦሪት ዘዳግም 16፥16 ላይ አንድ ላይ ተጠቕሰዋል … በተናጠል ደሞ ብዙ ቦታ) ከነዚህ መሀል አንዳቸውም ልክ ባይብል ላይ ይከበሩ በነበሩበት መልኩ በእናንተ ዘንድ አይከበሩም። እንደውም አብዛኞቻችሁ ስለነዚህ በዓላት አታውቑም። በነገራችን ላይ ኢየሱስም በምድር ቖይታው የፋሲካን (የቂጣ በዓል) እና የዳስ በዓልን እንደታደመ ባይብል ያስተምራል። ከዛ ውጪ አሁን እምታከብሯቸውን በዓላት ኢየሱስ አላከበረም … ሐዋርያትም አላከበሩም … ከሐዋርያት ኋላ የነበሩ እውነተኛ ክርስቲያኖችም አላከበሩትም።
ያው በዚህ መልኩ እውነተኛ የሆነው የክርስትና እምነት በብዙ ሰርጎ ገቦች ስለተበረዘ ክርስቶስ ያስተማረው ትክክለኛ የክርስትና አስተምህሮ የቱ ነው እሚለው ላይ ጥናት አርጉ ለማለት ያህል ነው።
የምግብ የመጠጥ የመስከር በዓል አለፈ
ከባብ ቼላል እትዮፕያ ገባ እዴ
ግርም የሚለኝ አገላለፃችሁ ጉዳት ማስተናገዱን ስትሉ? እኛ እግዳ ሲስተናገድጂ ጉዱት (አደጋ) ሲስተናገድ አይተንም ሰምተንም አናውቅም
A nation that celebrates holidays to the level of burning down its home up on itself, and drink till throwing oneself from cliff. So hot a celebration.
Yareju Yakebele betochin awkew eyakatelu Addis maserat bajil eyehona naw mengist linaka yigebal
Yamat bal bagina doro yatu sawoch lelochin lemawak hon bilaw esat eyelekosu naw ewnatachawn naw
ምነው እኔን እረሱኝ ሰክሬ ቀን 6ሰዓት ላይ
ትቦ የገባሁ አሁን ከምሽቱ 2ሠዓት ላይ
አይደለ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከትቦው
አውጥተው እራሴን ሆስፒታል ያገኘሁት
ምነው የኔን የማዘግቡት እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁ
ይሀ የወያነ ነው ሴራ ነው እመኑኝ
ከዚህ ውጭ ሌላ ጉዳት የለም ካላችሁ ጉዳት ምን ማለት እንደሆነ አልተረዳችሁም።
ምን አለ በሀገር የተለኮሰው እሳት እንዲሁ በጠፋ፡፡
Fana tv የዳይሜንድ ስፎንሰር ዋልያ ቢራ፡፡
እንድ እያደረጋቹ ቱቦ ስያንስ ነዉ
ሰካራም ቤት አይሰራም አላያችሁት ሁኖ ነውጂ ህጊዜ ብዙ ጠጭ ትቦ ውስጥ ገብቷን
Comments are closed.