Home Ethiopian News Seyoum Teshome Attacked – U.S. on Tigray & Eritrea – Ethiopian News March 27, 2021

Seyoum Teshome Attacked – U.S. on Tigray & Eritrea – Ethiopian News March 27, 2021

by Addis Media
2 comments

Seyoum Teshome Attacked – U.S. on Tigray & Eritrea – Ethiopian News March 27, 2021



Seyoum Teshome Attacked – U.S. on Tigray & Eritrea – Ethiopian News March 27, 2021
Watch daily updated Ethiopian news from a reliable and balanced source. Addis Media is an independent Ethiopian related News and other programs, producer.
Visit us https://AddisMedia.net Subscribe to our channel to follow everything related to Ethiopia.
AddisMedia Daily Ethiopian News Source #EthiopianNews #AddisMedia #Ethiopia

Latest Ethiopian News source. Watch Ethiopian News everyday from the reliable source.

You may also like

2 comments

Mohamed Al-Sanady March 28, 2021 - 11:17 pm

We need to keep in mind that our freedom of speech ends where the freedom of others starts. Hence for every action there is equally proportional reaction. I would be surprised if nothing happened to him than something like this happened. Well, the logic is if you want to leave in peace, leave others in peace. What goes around comes around. What can I say more… do good and good comes to you… and vice versa. Salaam

Yosef Worku April 12, 2021 - 3:50 pm

#ጥብቅ መልእክት ይድረስ #ለስዩም ተሾመ፣
============
በቅድሚያ ጊዜ ወርቅ በሆነበት አገር ቁጭ ብዬ ስራ የፈታሁ ይመስል ላንተ ይህንን የምዘበዝብበት ዋና ምክንያት እንደ ታላቅ ወንድም ደግሞም ለአንተ ካለኝ ከፍተኛ ግምት የተነሳ መሆኑን እንድታውቅ።

በመቀጠል፣
ለመሆኑ አንተ ማነኝ ተላትላለህ? ፈረንጆቹ እንደሚሉት #Whistleblower who disclose "Government illegality, waste, and corruption" from adverse consequences related to their employment ነህ ወይስ #investigative journalist who systematically, in-depth, and original research and reporting, often involving the unearthing of secrets, heavy use of public records ነህ? ወይስ ሌላ ነኝ የምትለው አለህ?

ሀገራዊ ቅናት፣
ለእውነት ለፍትህና ለእኩልነት መቆምህ ለኢትዮጵያዊ እጅግ የሚፈለግ ምግባር ነው። በተለይም #ምሁራን ፈሪዎችና አድርባዮች በሆኑባት በኢትዮጵያ ያንተ ጥረት የሚደነቅ ብቻ ሳይሆን ለወጣቱ አርአያ የሚሆን ነው። ስለሆነም እንዳንተ ያሉ #በእውነት-እና-በእውቀት የሚሰሩ ዜጎች ይበዙልን ዘንድ ለማበረታታት ፎቶህን ከምስጋናና የማበረታቻ ቃል ጋር በፔጄ ላይ ፓስት ካደረግሁ ሰነበትሁ።

#መፅሀፍ ቅዱስ
"ከጠላት #መሳም ይልቅ የወዳጅ #ንክሻ" ይሻላል እንደሚል፣ የምትተቻቸው ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶችና ግለሰቦች፣ ስዩም የሚተቸን ለሀገራችን ዘላቂ ጠቀሜታ በማሰብ፣ ደግሞም እኛንም ከጥፋት መንገድ ለመመለስ በቅንነት ነው ብለው ቢቀበሉህ መልካም ነበረ፣ #ነገርግን አይደለም።

ከአትሌቶችና፣
አንዳንድ እንደነ ቴዲ አፍሮ ያሉ አርቲስቶቹ በስተቀር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በሀቅ መንገድ ሀብት ያከማቹ ሚሊየነሮች (ባለስልጣናቱና ነጋዴዎችን ጨምሮ) ምናልባትም 1% እንኳን ስለማይሞሉ፣ 99% በሙሉ ህወሓትን ተጠግቶ "ሀብት" ያከማቸ ዘራፊ ሌባ በመሆኑ በተቸኸው መጠን ስዩምን እንዴትና መቼ እናስወግደው፣ እንግደለው ብለው የሚያስቡ መሆናቸውን ላፍታም ከተዘናጋህ አዋቂ ነገር ግን ጅል ደፋር እንጂ ምንም አትባልም።

"#ጥንቃቄ ይጠብቅሀል ማስተዋልም ይጋርድሀል"፣
እንደሚል ህያው መፅሀፍ የምታቀርባቸው እውነት ቢሞላባቸውም፣ በጥንቃቄና በማስተዋል ካላደረግኸው በስተቀር፣ በግል የምታጠቃቸው የሚመስላቸው ሰዎች በእጅ አዙር #እስከሞት የሚያደርስ ጥቃት ሊያደርሱብህ እንደሚችሉ እያወቅህ #በፍርሀት ሳይሆን #በጥበብ ባትመላለስና ብዙ መስራት ስትችል አደጋ ቢደርስብህ #ጀግና ሳትሆን እውነትም የጅል #ጅል ነህ።

ጀግና፣
ደፋር ብቻ ሳይሆን ብልህም ነው። "እንደ እባብ ብልህ እንደ ርግብ የዋህ ሁን" የሚልህ መፅሀፍ ቅዱስ ለዚህ ነው። በመሆኑም ረጅም አመታት አገሬን ህዝቤን በእውቀትና በእውነት በጥበብ እየተመራሁ አገለግላለሁ የምትል ከሆነ? #ባለስልጣን ወይም ባለሀብት #ሌባና ዘረፊና ነፍሰገዳይ መሆኑን ብታውቅም እንኳን #በፍርድ ቤት ካልተረጋገጠ ድረስ [innocent until proven guilty] #በየስማቸው እየጠራህ #ማንጓጠጥና ማጋለጡ ከህግ አኳያ ቢያንስ #በስም ማጥፋት ደረጃ የሚያስጠይቅ ስለሆነ፣ የሕግ አዋቂዎችን እያማከርህ መስራት የውዴታ ግዴታህ ነው። #ማስረጃና መረጃ ያገኘህበት በአሻጥር የተሞላ መ/ቤትን እንኳን በሚዲያ እንዴት እንደምትገልፅ አሁንም የሕግ ሰዎችን በማማከር ነው መስራት ያለብህ።

ኣኣይ አልፈልግም፣
እንደፈለግሁ እሆናለሁ "ውርድ ከራሴ" ካልክም "የጅል በትር ሆድ ይቀትር" ብለን፣ የቱንም ያህል ስራህን ብናደንቅ "አይ የስዩም ነገር ስንት መስራት ሲችል በጥበብ መመላለስ አቅቶት እንደ ዋዛ ሞቶ ቀረ" ብለን አዝነን እንተውሀለን።
………………………..
#በመጨረሻም
አንድ ሁለት ነጥቦችን ልተውልህ፣
1ኛ/ እነዚህን ያንተን በእውነትና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ዕይታዎች አስቀድመህ ለጠ/ሚሩ ወይም ለአማካሪዎቻቸው ብታቀርበውስ? በሰለጠነው አለም ለመሪዎች በየቀኑ የሚደረግ briefing አለ፣ የአገሪቱ መሪም ይህንን መስማትና ማስካከል ኃላፊነቱና ግዴታው ነው።

2ኛ/ የቃላትን አጠቃቀምህ በፕሮፌሽናል አቀራረብ እንጂ እልህና ንዴት በተሞላበት ድምፀት መሆን የለበትም፣ ወይም ለህዝብ ጥቆማ Informative approach ብትቀርብ የበለጠ ጠቃሚ ነው።

3ኛ/ ባለሁበት እቀጥላለሁ ካልክም፣ በ Investigative journalist ማእረግ የመንግስት ሙሉ ጥበቃ 24/7 እየተደረገልህ መሆን አለበት።

አለበለዚያ፣
ዛሬ በከንቱ ተደበደብክ! ነገ ደሞ ሞት ይደግሱልሀል። ከዚያ በኋላ "አይ ስዩም! ባጭሩ ተቀጨ! ጎበዝ አዋቂ ጠያቂ፣ በእውነት እና በእውቀት የሚሰራ ነበረ፣ ምን-ያደረግ አጉል ደፋርና-ጅል ሆኖ ሰለተገኘ ባጭሩ ተቀጨ እንጂ" ይባለና forever ትረሳለህ።

4ኛ/ #ፊደል ወይም እውቀት (ብቻውን) ይገድላል መንፈስ (ማስተዋል/ጥበብ የሞላበት) ግን #ያድናል፣ እንደሚል መጽሀፍ ቅዱስ፣ ብዙ መረጃ-ነክ #እውነትና #የንባብ/እውቀት በማብዛትህ ምክንያት ብዙ ሀዘን በራስ ላይ የጨመርህ በመሆኑ ከዐቢይ አህመድ እና ከሀጂ ሙፍቲ በስተቀር ሌሎች ሰዎችን ሁሉ እንደ ጠላት የማድረግ አባዜ የተጠናወተህ አያዛልቅም። ይህን መሳይ አካሄድህ አያዋጣምና የበለጠ እንድታገለግል ሁሉንም ነገር እንደየጊዜው በጥበብ መያዝና መስራት ያስፈልግሀል።

#የዐቢይን ባለስልጣናትን፣
ሁሉ ማውረድ በሚመሰል አቀራረብ በስም እየጠራህ ማጋለጥ፣ ወንጀለኞች መሆናቸው በኋላ ላይ ቢረጋገጥ እንኳን፣ ያንተ አቀራረብ እንዲበረግጉ በማድረግ የባሰ ውስብስብ ችግሮች ባገሪትዋ ላይ የሚጋበዝ እንጂ የሚረዳ አይደለም ።

#ወዳጄ ስዩም ተሾመ፣
#ፓትሪክ ሉቡምባና #ክዋሜ ንኩሩማ የሚያክሉ የአፍሪካ ጭንቅላቶች፣ እውነትና እውቀት ቢሞላባቸውም፣ በጥበብና በማስተዋል በመመላለስ፣ ፍትህና የኢኮኖሚ እኩልነት ከማስፍን ይልቅ፣ በእልህና በቁጭት፣ በግልፅና በድፍረት በመናገር በመስራታቸው ነው፣ በራሳቸው ወገኖች በእጅ አዙር በእድሜቸው አጋማሽ ላይ ባጭሩ በሞት የተቀጩት። ይህንን መናገሬ፣ እንደትፈራ ሳይሆን እንድትጠነቀቅ ከመፈለጌ ብቻ መሆኑን እንዳትርሳ።

#ይህንን ሁሉ የምልህ፣
"#ስዩሜ ጎበዝ ጀግና አይዞህ በርታ" ብቻ ከሚሉህ #አላዋቂ ወይም የማያስተውሉ ብዙ ሺ ወዳጆችህ፣ ወይም ደግሞ እያወቁ ወዳጅ ከሚመስሉ ጠላቶችህ ይልቅ፣ "ከጠላት መሳም የወዳጅ ንክሻ ይሻላል" የሚል የመጽሀፍ ቅዱስ መርህ ተከትዬ የምተችህ የእኔ ለዘለቄታው ይበጅሀል። ባጭሩ ይኸው ነው!

እግዚአብሔር ማስተዋልና ጥበብ ይሙላብህ!

Comments are closed.

About Us

AddisDaily is an Ethiopian News and related topics provider website.  Find our daily updated Ethiopian News on our YouTube channel. @Addis_Daily

 

©2025 AddisDaily.com, A Digital Media Company – All Rights Reserved. Designed and Developed by AddisSolultions.com