Home News ለቸኮለ! የዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 24/2011 አበይት ዜናዎች- ከዋዜማ ራዲዮ

ለቸኮለ! የዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 24/2011 አበይት ዜናዎች- ከዋዜማ ራዲዮ

by AddisDaily
13 comments

ለቸኮለ! የዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 24/2011 አበይት ዜናዎች- ከዋዜማ ራዲዮ

1. ንጉሡ ጥላሁን የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚንስትር ጸህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም እና ምክትላቸው ሄለን ዮሴፍ ዛሬ ከሃላፊነት ተነስተዋል ሲል ፋና ዘግቧል፡፡ በሄለን ምትክ ደሞ ካሳሁን ጎፌ ተተክተዋል፡፡ ንጉሡ ቀደም ሲል የአማራ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ባሁኑ ሰዓት ደሞ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ናቸው፡፡ የኦዴፓው ካሳሁን ደሞ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስትር ደዔታ ሆነው አገልለዋል፡፡ አዲስ ስታንዳርድ አመሻሹን ባስነበበው ዘገባ ግን ቢልለኔ ስዩምና ሄለን ዮሴፍ በሀላፊነታቸው ይቀጥላሉ፣ አቶ ንጉሡ የፕሬስ ፅህፈት ቤቱ ሀለፊ መሆን የቀሪዎቹን የስልጣን ድርሻ አይነካም ብሏል። የካሳሁን ጎፌ ሹመትንም ሀሰት ነው ብሏል ዘገባው።

2. የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ይ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ በ3 ቀናት ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከአቻቸው ወርቅነህ ገበየሁና ከአፍሪካ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ፡፡ በመቀጠልም ለተመሳሳይ ጉብኝት ወደ ቡርኪና ፋሶ፣ ሴኔጋል እና ጋምቢያ ያደርጋሉ፡፡

3. በአማራ ክልል በኮማንደር ውበቱ ሽፈራው ቤት ውስጥ የተያዙትን ሕገ ወጥ ሽጉጦች ወደተለያዩ ቦታዎች ለማሰራጨት ታቅዶ እንደነበር የክልሉ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ ሃላፊ ተናግረዋል፡፡ ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ለDW እንዳሉት ሽጉጦቹ አዲስ እና ቱርክ ሰራሽ ናቸው፡፡ ወንጀሉ ባንድ ሰው ብቻ የተፈጸመ አይመስለንም፤ ተባባሪዎች እንደሚኖሩ ስለምንጠረጥር ክትትል እያደረግን ነው ብለዋል፡፡ ተጠርጣሪው የክልሉ ልዩ ጥበቃ ፖሊስ አዛዥ ናቸው፡፡

4. በደቡብ ክልል ካፋ ዞን፣ ደቻ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ 9 ሰዎች በድንገተኛ ጥቃት ተገድለዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ባንድ ሠፈራ ጣቢያ ውስጥ መሆኑን ሪፖርተር የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ አስነብቧል፡፡ በጥቃቱ ሌሎች 4 ሰዎች ክፉኛ ተጎድተዋል፤ ብዙ ንብረትም ወድሟል፡፡ ጥቃት አድራሾቹ ከዞኑ ጠረፋማ አካባቢዎች ወይም ከአጎራባቾቹ ቤንች ማጂና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የመጡ መዔኒት የተባሉ አርብቶ አደር ጎሳ አባላት እንደሆኑ ተገምቷል፡፡

5. መንግሥት መጭውን የገና በዐል በማስመልከት ለ530 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል፡፡ በተለይ ሕጻናት ልጆች ያሏቸው ሴት ፍርደኞች ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል- ብለዋል የጠቅላይ ዐቃቤ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዝናቡ ቱኑ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፡፡ የይቅርታው ተጠቃሚዎች በዐቃቤ ሕግ ስር በፌደራልና ክልል ወህኒ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች ናቸው፡፡ ባለፈው ዐመት የምህረት አዋጅ ሥራ ላይ ከዋለ ወዲህ ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች ምህረት አግኝተዋል፡፡

በሌላ ዜና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በቡራዩ ጥቃት እንደተሳተፉ በጠረጠራቸው 109 ግለሰቦች ላይ ዛሬ ክስ መመስረቱን ተናግሯል፡፡ ከእነዚህ መካከል 28 በሌሉበት ክስ የተመሠረተባቸው ናቸው፡፡

6. በታንዛኒያ 14 ኢትዮጵያዊያን መኪና ውስጥ ተፋፍገው መሞታቸው ተነግሯል፡፡ ሟቾቹ በዛምቢያ ወይም በማላዊ በኩል አቋርጠው ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ያለሙ ስደተኞች ሊሆኑ እንደሚችሉ የሀገሪቱ ፖሊስ ገልጧል፡፡

7. ሱዳን ውስጥ ሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ያገቷቸው 16 ኢትዮጵያዊያን ተለቀዋል፡፡ ታጋች ስደተኞቹ የተለቀቁት የሱዳን ጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የሃይል ርምጃ መሆኑን ሸገር ዘግቧል፡፡ አሁን በካርቱም የኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ለሌሎች ያጋሩ SHARE SHARE

Source: Wazema Radio ዋዜማ ሬዲዮ Facebook

You may also like

13 comments

Semeru Yimer Yimer January 2, 2019 - 9:40 am

Tnx!

Ahmed Ezedin January 2, 2019 - 9:54 am

ዋዜማችን የኛ የመረጃ ምንጫችን እናመሰግናለን

Get Net Sun January 2, 2019 - 10:05 am

ቢልለኔ ፍጹም ሳይሆን ቢልለኔ ሥዩም ነው።

Ahmed Kebede January 2, 2019 - 10:08 am

Thank you so much, dears!

Temesgen Berfay January 2, 2019 - 10:30 am

Really information source wazema

Abulaa Yehalango Megisolij January 2, 2019 - 11:03 am

በከፋ ዞን የሞቱት ከከምባታ ጠምባሮ ዞን የሄዱ ሰፋርዎች ስሆኑ ፈራሹ ክልል ደቡብ እና አዉሬዉ ፓርት ደኢህዴን መጠበቅም ሆነ የሀዘን መግለጫ መዉጣት አለመቻሉ አሰዝኖናል። ለማን አቤት ይባል ይሆን?

Baru Fatene January 2, 2019 - 11:39 am

ደቡብ።ክልል።ከፈ።ዞን።ደኘ።ወረደ።9ሰዎች።በምን።አደገነዉ።የጎችሁ

Nahom Ayele January 2, 2019 - 12:30 pm

አቶ ንጉሡ ጥላሁን በሚል ይስተካከል ሌላ ጣጣ አታምጡብን ??

Aman Yhun January 2, 2019 - 1:23 pm

እናመሰግናለን

Zeleke Tamiru January 2, 2019 - 1:47 pm

thank u but stop using the word ደሞ instad of ደግሞ

Yihenew Alebet January 2, 2019 - 2:29 pm

Thankyou

Sisay Shiferu Yadate January 2, 2019 - 5:17 pm

Thanks

Dag Marley January 3, 2019 - 6:47 am

ከያቺ ነገር ቀጥሎ ሱሴ ዋዜማዎች ሆናችዋል። ፈጣን፦ ተደራሽ፦ ትኩስና ወቅታዊ መረጃ ለሰፊዉ ማ/ሰብ ተጨንቃችሁና ተጠባችሁ ለምታደርሱን መረጃ ከልቤ አመሰግናለዉ!!!

Comments are closed.

About Us

AddisDaily is an Ethiopian News and related topics provider website.  Find our daily updated Ethiopian News on our YouTube channel. @Addis_Daily

 

©2025 AddisDaily.com, A Digital Media Company – All Rights Reserved. Designed and Developed by AddisSolultions.com